Amharisk
እንኳን ወደ ከረንሰ NoTe Norwegian Teaching የኢንተርኔት ትምህርትቤት በሰላም መጣቹ። በ NoTe የኖርዌጅያን ቋንቋ ኮርሶች በ ኢንተርኔት (norskkurs på nett) በሁሉም ደረጃ ይሰጣል። የምንሰጣቸው ኮርሶች ከዝቅተኛ (norskprøve) እስከ ከፍተኛ ደረጃ(Bergenstesten) ለሚሰጡ የብቃት መመዘኛ ፈተናዎችን በብቃት ያዘጋጃል። እንዲሁም በኖርዌጂያን ኢሚግሬሽን ዳይሮክተሬት(UDI) እና የኖርዌይ የጎልማሶች ትምህርት ተቋም(Komptense Norge) ተቀባይነት አለው። ኮርሶቹ የሚሰጡት የ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ኖርዌጅያን በሆኑ እና ከኖርዌጅያን ቋንቋ ማስተማር ጋር በተለያዩ መንገዶች ለረጅም ጊዜ ልምድ ባካበቱ ብቁ መምህራን ነው ፡፡
በኢንተርኔት የሚሰጡ ኮርሶች ምቹነት
ኮርሶቻችን በኦንላይን የሚሰጡ በመሆናቸው ምቹ ናቸው። በማነኛውም ጊዜ እና በፈለጉት ቦታ! ትምህርቶቹ በሁሉም የኑሮ ሁኔታዎች ውስጥ ላሉ፣ በሥራ የተጠመዱም ሆኑ ብዙ የሚሰሩ ፣ በቤት ውስጥ ላሉም ሆኑ ተማሪ ተስማሚ ናቸው ፡፡
የምንሰጣቸው ኮርሶች በደረጃ A1 ፣ A2 ፣ B1 ፣ B2 እና C1 ናቸው። ባልዎት የቋንቋ እውቀት ደረጃ መሰረት ከተጠቀሱት የደረጃ አይነቶች መርጠው ኮርሶቹ መጀመር ይችላሉ። በኮርሶቹ ውጤታማ ለመሆን በየቀኑ ከ2-3 ሰዓታት ጊዜ እንዲሰጡ እንመክራለን ፡፡
እንዲሁም፣ በጤናው ዘርፍ እና በመውአለህፃናት ውስጥ ለሚሰሩ የጤና እና የመውአለህፃናት የኖርዌጂያን ቋንቋ ኮርሶች አሉን ፡፡ በተጨማሪም ፣ የኖርዌጅያን ቋንቋ የመናገር ክህሎትን ለማሻሻል ለሚፈልጉ የውይይት ሥልጠና እንሰጣለን ፡፡
የ 50 ሰዓታት የማህበራዊ ትምህርትን (Samfunnskunskapskurs) ለሚወስዱ ሰዎች ፣ በኖርዌጅያን ፣ በአረብኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንሰጣለን።
ብቁ መምህራን እና ጥራት ያላቸው ኮርሶች
የኦንላይን ትምህርት ቤቱ የተጀመረው እ.ኤ.አ. በ 2015 ነው፡፡ ከረንሰ ከ 15 ዓመታት በላይ የኖርዌጅያን ቋንቋ የማስተማር ልምዷን በመጠቀም ውጤታማ የሆነ የኦንላይን ኮርሶችን ለማዛጋጀት በቅታለች።
የኦንላይን ትምህርት ቤቱ ተማሪዎቻችንን ድጋፍ የሚሰጡ ብቃት ያላቸው የኖርዌጅያን ቋንቋ መምህራን ቡድን አለው፡፡ ከኦንላይን ኮርሶች ጎንለጎን በተጨማሪ በ ነፃ የሚሰጡ የከረንሰ የ ዩቱብ ቪዲዮዎችን ፣ ፖድካስቶችን ፣ የድምፅ መልዕክቶችን ፣ የኢንስታግራም አካውንት እና የፌስቡክ ቡድንን(Facebook group) መጠቀም ይችላሉ ፡፡
ስለ የተለያዩ ቻነሎቻችን ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ማስፈንጠርያ ይጫኑ
ኮርሶቹ ከግል እገዛ ጋር
የኖርዌጅያን ቋንቋ የ ኦንላይን ትምህርቶቹ ንባብን ፣ ማዳመጥን ፣ የጽሑፍ መልመጃዎቻችን እና የድምፅ ቀረጻዎችን ያካትታሉ ፡፡ የሚረከቡ የጽሑፍ መልመጃዎቻችን በአስተማሪዎቻችን የሚነበቡ ፣ የሚታረሙ እና የሚገመገሙ ናቸው ፡፡ከዚህም ለሚቀጥለው ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ተጨማሪ ምክሮችን ያገኛሉ፡፡
እያንዳንዱ ኮርስ ምን ምን እንደምያካትት ለማወቅ ተጨማሪ ያንብቡ ወይም ኢሜል ይላኩልን።
በኮርሱ የተካተተ በየወሩ የ 1 ሰአት ከአስተማሪ ጋር የዉይይት መድረክ አለን። በነዚህ ሰአታት መጻፍ እና ማንበብ ብቻ ሳይሆን በተሻለ ሁኔታ የኖርዌጅያን ቋንቋ ለመናገር የቃላት አጠራርዎን፣ የት ቦታ ማሻሻል እንዳለብዎት የሚጠቅሙ የቋንቋ የመናገር ልምምድ ያደርጋሉ። ከዚህም በተጨማሪ አንድ ሰአትዋን የሚያጠራጥርዎ የሰዋሰው ወይም የቃላት አገባብ ዘይቤን፣ ወይም ለስራ ቃለመጠየቅ ራስዎን በማዘጋጀት ዙሪያ ላይ ወዘተ መወያየት የችላሉ።
የውይይት መድረኩን ካጠናቀቁ በኋላ፣ በውይይት መድረኩ ያገኙትን እውቀት፣ መለማመድ ያለብዎትን ቃላቶች እና ለዚሁ የሚያግዙ ጠቃሚ የሆኑ የመረጃ ደህረ ገጾችን ያጠቃለለ የወይይት ሰነድ ያገኛሉ።
የ እንግሊዘኛ ቋንቋ ኮርሶች በ ሁሉም ደረጃ
በ NoTe የእንግሊዘኛ ቋንቋ ኮርሶችን በ ሁሉም ደረጃ የሰጣል፤ የቢዝነስ ቋንቋን ጨምሮ። ከ 1 እስከ 6 ወር የሚዘልቅ የኦንላይን ኮርሶች አሉን፣ እስከ ደረጃ B1። የህንን ደረጃ ሲጨርሱ ቀጣይ ከፍተኛ ደርጃ ኮርሶችን መማር ከፈለጉ ተጨማሪ ሰአት ከመምህርዎ ጋር በመነጋገር መመዝገብ የችላሉ።
የ እንግሊዝኛ ቋንቋ ኮርሶቹ እንግሊዘኛ ቋንቋን ማወቅ ለሚፈለግ ብቻ ሳይሆን፣ ውጭ ሃገር ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ሂደው መማር ለሚፈልጉ በዚህም መክንያት የ TOEFL-test ወይም IELTS-test የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተናዎችን መውሰድ ለሚፈልጉ በብቃት የምያዘጋጁ ናቸው።
የ እንግሊዝኛ ኮርሱን የሚያስተምሩ አስተማሪዎቻችን ከ አሜሪካ የመጡ በ ኖርዋይ የሚኖሩ መምህራን ናቸው።
ከ ከረንሰ ጋር ይተዋወቁ
ሰለ ኦንላይን ኮርሶችን የ ከረንሰ የ ዩትዩብ ቻነል ላይ በጥቂቱ መቋደስ ይችላሉ።
የኦንላይን ኮርሶቻችን ምን እንደሚመስሉ ለማወቅ ይህንን ቪድዮ ይመልከቱ:-
ይመዝገቡ
አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ ነን። በየትኛውም ደረጃ ቢሆኑም፣ ወደፊት ወደ ሚፈልጉበት ደረጃ ለመድረስ ለሚፈልጉ ሁሉ በደስታ እንቀበላለን።ግባችን እርስዎ በ ኖርዌጅያን ቋንቋ ብቁ እንዲሆኑ ነው።